Posts

ማቴ ፳፪፥፴፱

መጽሐፍ እንዲህ ይላል   “ዝንቱ ትእዛዝየ ውእቱ አፍቅር ቢጸ… .ትእዛዜ ይህቺ ናት ባልጀራህን እንደነፍስህ ውደድ የምትለዋ” ማቴ ፳፪፥፴፱

ኃያል አምላክ

Image
እግሬ እንደሚራመድና እጆቼ ግድጊዳ እየተደገፉ ጉዞ መቀጠሌን አስታውሳለሁ፡፡ ‘ሳይደግስ አይጣላም’ እንደሚሉት ይመስለኛል በጉዞዬ መሐል ከቅርብ የቤተክርስቲያን ጉልላት ይታየኛል፡፡ አንዳች ስበት ጎትቶኝም ደርሼ ገባሁ፡፡ ከዛፍ ስር ተቀምጬ የአንገት ልብሴ እስኪርስ ድረስ አነባሁ፡፡ አይኖቼን አላዘዝኳቸውም ዝም ብለው ያፈልቃሉ-ትኩስ ውኃ፡፡ እስኪበቃው ድረስ አይኔ ማንባቱን ቀጠለ፡፡ አዕምሮዬ ውል ያለው ነገር ባያስብም ቅሉ እያነባሁ በሐሳብ እከላወስ ነበር፡፡ በእንባዎቼ ታግዞ ተዝቆ የወጣለት ይመስል ቀለል ሲለኝ ይሰማኛል፡፡ ፊት ለፊቴ የሚታየኝ የመቅደሱ ጉልላትና መስቀሉ ነበር ከዛ በላይ ሰማይ………… በሰማይም አንድ ኃይል…..የማይተው የማይረሳ ፈጽሞ የማይዘነጋ ዘወትር አለሁኝ የሚል ልዕለ ኃያል አምላክ፡፡

የዘመን ኅዳግ

መታሰቢያ  ይሁን ዘመን ለጠፋው ዘ መን ከኮሮጆው ከማደሪያው ገባ እጥፋት አበጀ ምዕቱን ከምዕት ሺህውን በሺህ አጥፍቶ ጥንተቱን አወጀ ከዘመኑ ድንበር ከማማው ላይ ቆሞ                      ልባሙ፡ ሕይወት እየሳለ ምልሰቱን ጀመረ “ ዘመኑ ገር ሞልቶት ጥጋብ ትርጉም አ’ቶ ሰልጥኖ ነበረ ብዙዎች ተኝተው ሲያንኮራፉ ሳለ ከዚ’ች ሃገር ላይ እንቅልፍ ተሰደደ ሁሉም እየተጋ በእውቀት ሲታነጽ                     በአስተሳሰብ ልቆ በፈጠራ መጥቆ ከ’ድገት ተዋለደ ማጀቱ ሞልቶለት እያደለ ሲሰጥ ለጋስ ደግ ተባለ የቅን ሐገር ንጉስ ዓይኖች አንጋጠው፣ እጆች ተዘርግተው ንጉስ ሲማጸኑ ከበሬታ ሲፈስ ሰብተናል ብላን፣ አፈራን ቅጠፈን ተማጽኖ ሲበዛ መሪነትን ያዘ ፊት ‘የቀደመ ጎረቤቶቹ ላይ ኃይሉ ‘የበረታ ክንዱ ‘የረዘመ ድምጹ አስገመገመ፡፡ ክብር በክብር ላይ ሞገስ በሞገስ ላይ ህዝቡ ‘የበዛለት ዝናው ባለም ናኘ ዓለምን ለመምራት ከቢጤዎቹ ጋር ሥልጣን ተቆራኘ፡፡ አቅሙ እየዳበረ ፋና ወጊ ሆነ                አግዓዚ ኃይሉ ዓለም እየመራ ድንቅ እየከሰተ ‘ደውቂያኖስ ጠርዝ ድንበሩ እየሰፋ          ...

ናፍቆቴ ነበርሽ…

የዘመን ድልድዬ … ተስፋ እየመገብሽኝ ጣዕምሽ አልባሴ ….. ፍቅርሽ ኑሮ ሆነኝ፡፡ በኑሮሽ ታዛ ስኖር ተጠግቼ ረሃብ ጠግቤ በጥማት ረክቼ እያለምኩሽ ነበር ገላሽን ጓጓቼ፡፡ እድሜን የሚያረዝመው የገላሽ ውበቱ ክንድን የሚያፋፋው የሚፋጅ ሙቀቱ ንጉስ ከናሽከሩ እተቧጠረ ይታደስበታል ክብርሽ በየአልጋው እየተደፈረ ተጋልጦ ይታያል ያቀፈም የተኛም ለገላሽ ዘብ ሁኖ ይዋደቅለታል፡፡ አይኔ እስኪጨልም፣ የምኞት ባዘቶ አቅሌን እስኪሰውር ምላሴ ተቧጦ አፌ እስኪዘጋ እጄ እስኪቆረጥ እግሬ እስኪታሰር ናፍቆቴ ስለሆንሽ ህልሜን አንቺ አደረኩ አብሬሽ ለመኖር፡፡ ለፍኩት ገላዬ ለደረቀ ጠጉሬም ህልሜን እየቀባሁ የወየበ ቆሽቴን የታጠፈ አንጀቴን በተስፋሽ እያሰርሁ መኖርሽ ‘ዳይጠፋ ውበትሽ እንዳይከስም ወዜን ቀባሻለሁ፡፡ እኔ ብዙ ስሆን የገላሽ ባይተዋር ቀንሽን ‘ምቆጥር ‘ሚተኛሽ አንድ ነው ሙቀትሽ ያፋፋው ቀኔን የሚቆጥር አንዱ … ክብር ይቆፍራል፣ እድሜውን ያረዝማል ብዙው … ክብርሽን ይሞላል፣ እድሜውን ይቆርጣል፡፡ አሁን ግን ናፍቆቴ…… ትዝታሽ በዛና ከናፍቆትሽ ቀድሞ በቁም አፈዘዘኝ የገላሽ ውልብታ ያብሮ መኖር ትልሜ ዛሬ አይታየኝ ምነው ባላወኩሽ የልጅነት ፍቅሬ እናቴ በቅታልኝ አፌ ከተዘጋ ዐይኔም ከሟሟ ጣቴም ከተለየኝ እግሬ ከታሰረ ህልሜን ከተቀማው እእምሮ ከራደኝ አሁን ትዝታ ነሽ ድልድይ ሁነሽልኝ ዘመን ‘ማታሳዪ አሁን ትዝታ ነሽ ኑሮዬን ልታድሽ ጥላቻ ‘ምትሞዪ ተስፋን ‘ዳትግችኝ ሰውነቴ ጠፍቶሽ ከተኛሽ ‘ምትደክሚ በናፍቆቴ መግል ወዜን እየጠባሽ የምታገግሚ፡፡ ዳሩ…. እኔ ብዙ የሆንኩ መቀመጤ ስቃይ መሄዴም ያቆስላል አንድ የሆነ እርሱ መኖሬን ሲያጨልም ናፍቆቴን ሰውቷል፡፡

እኛ ..... በትግስት ማሞ

ን’ጎርሰው ሳይኖረን እኖረው ሳይኖረን ባዶ ተስፋ መሐል መጪውን ሞሽረን የሰጡንን ቀምሰን ባሉን አሜን ብለን ባንድዬ ቸርነት አይችሉትን ችለን ተገፍቶ የማያልቅ ጉድ ዘመን ተሻግረን ይኸው ዛሬም አለን ህልማችን መሐል ላይ ስደት ተስሎበት በልባችን ሙሉ ራስ መውደድ በቅሎበት ኑሯችን ጫፉ ላይ ፍርሃት ቋጥረንበት እምኝ ብርቃችን ነው መዘመን ከሆነ አዎን ዘምነናል ፈሪ ለ’ናቱ ነው መፍራት ይሻለናል መሰልጠን ከሆነም አዎ ሰልጥነናል ሃገር ምንያደርጋል ትውልድ ምናባቱ እኔነት መርጠናል አዎን ሰልጥነናል አዎን ሰይጥነናል የሰው ሰርግ አድማቂ አጃቢ ሆነናል ሕይወቱን የጠላ አንድ ሞኝ ምስኪን ሰው ደፋር እስኪመጣ ተስፋችንን በፍራት ትውልዱን በፍዘት በግፍ የምንቀጣ ዛሬ በልቶ ማደር የህሊናችንን ሚዛኑን ያሳተን ተመሳስሎ ኑሮ አጨብጭቦ ሹመት በባርነት ስለት የሚበላልተን የሚዶላልተን የምንኖር መሳይ የሆነልን መሳይ የምንቆም ሞተን እንደዚያ ነን እኛ

#ኦሮማይ ..... በበአሉ ግርማ

ከጎራው ዘልቄ እስኪ ልነጋገር ካለሰው ቢወዱት ምንያደርጋል ሃገር? የኔ ውብ ከተማ ህንጻ መች ሆነና የድንጋይ ክምር የኔ ውብ ከተማ መንገድ መች ሆነና የድንጋይ አጥር የኔ ውብ ከተማ የኔ ውብ አገር የሰው ልጅ ልብ ነው የሌለው ዳርቻ የሌለው ድንበር፡፡ ህንጻው ምን ቢረዝም ምን ቢጸዳ ቤቱ መንገዱ ቢሰፋ ቢንጣለል አስፋልቱ ሰው በሰው ካልሸተተ ምንድነው ውበቱ? የሰውን ልብ ነው! ምን ቢነድ ከተማው ተንቦግቡጎ ቢጦፍ ቢሞላ መንገዱ በሺህ ብርሃን ኩሬ በሺህ ብርሃን ጎርፍ ምን ያደርጋል? ምን ያሳያል? ካለሰው ልብ ብርሃን ያ ዘላለማዊ ነበልባል ያ ተስፋ ሻማ ጨለማ ነው ሁሌም ጨላማ!