በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የኢትዮጵያ ስም በጥቂቱ የሚከትሉትን ጥቅሶች ያንብቡአቸው
ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች። መዝሙረ ዳዊት 68፥31
በውኑ ኢትዮጵያ ዊ መልኩን ወይስ ነብር ዝንጕርጕርነትን ይለውጥ ዘንድ ይችላልን? ትንቢተ ኤርምያስ13፥23 ህንደኬ የተባለች የኢትዮጵያ ንግሥት አዛዥና ጃንደረባ የነበረ በገንዘብዋም ሁሉ የሠለጠነ አንድ የኢትዮጵያ ሰው ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ነበር፤ ሲመለስም በሰረገላ ተቀምጦ የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ያነብ ነበር። የሐዋርያት ሥራ 8፥27
የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን? ይላል እግዚአብሔር፦ ትንቢተ አሞጽ 9፥7
እግዚአብሔርም አለ፦ ባሪያዬ ኢሳይያስ በግብጽና በኢትዮጵያ ላይ ሦስት ዓመት ለምልክትና ለተአምራት ሊሆን ራቁቱንና ባዶ እግሩን እንደ ሄደ፥ እንዲሁ የአሦር ንጉሥ የግብጽንና የኢትዮጵያን ምርኮ፥ ጐበዛዝቱንና ሽማግሌዎቹን፥ ራቁታቸውንና ባዶ እግራቸውን አድርጎ ገላቸውንም ገልጦ፥ ለግብጽ ጕስቍልና ይነዳቸዋል። እነርሱም ከተስፋቸው ከኢትዮጵያከትምክሕታቸውም ከግብጽ የተነሣ ይፈራሉ ያፍሩማል ትንቢተ ኢሳይያስ 20፥3-5
በንጉሡም ቤት የነበረው ጃንደረባ ኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ ኤርምያስን በጕድጓዱ ውስጥ እንዳኖሩት ሰማ:: ትንቢተ ኤርምያስ 38፥7
እኔ የእስራኤል ቅዱስ አምላክህ እግዚአብሔር መድኃኒትህ ነኝ ግብጽን ለአንተ ቤዛ አድርጌ፥ ኢትዮጵያንና ሳባንም ለአንተ ፋንታ ሰጥቻለሁ። ትንቢተ ኢሳይያስ 43፥3
ንጉሡም ኢትዮጵያዊውን አቤሜሌክም። ከአንተ ጋር ሠላሳ ሰዎች ከዚህ ውሰድ፥ ነቢዩም ኤርምያስ ሳይሞት ከጕድጓድ አውጣው ብሎ አዘዘው። ትንቢተ ኤርምያስ 38፥10
የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ። ሂድ ለኢትዮጵያዊውምለአቤሜሌክ እንዲህ በለው። የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ለበጎነት ሳይሆን ለክፋት ቃሌን በዚህች ከተማ ላይ አመጣለሁ በዚያም ቀን በፊትህ ይፈጸማል። ትንቢተ ኤርምያስ 39፥16
የሁለተኛውም ወንዝ ስም ግዮን ነው እርሱምየኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከብባል። ኦሪት ዘፍጥረት 2፥13
ሙሴም ኢትዮጵያ ይቱን አግብቶአልና ባገባትበ ኢትዮጵያ ይቱ ምክንያት ማርያምና አሮን በእርሱ ላይ ተናገሩ። ኦሪት ዘኍልቍ 12፥1
ከእርሱም ጋር ከግብጽ ለመጣው ሕዝብ ቍጥር አልነበረውም እነርሱም የልብያ ሰዎች፥ ሱካውያን፥ የኢትዮጵያ ሰዎችም ነበሩ። መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 12፥3
ኢትዮጵያውያንና የልብያ ሰዎች እጅግ ብዙ ሰረገሎችና ፈረሰኞች የነበሩአቸው እጅግ ታላቅ ጭፍራ አልነበሩምን? መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 16፥8
ኢትዮጵያዊውም ዝሪ አንድ ሚሊዮን ሰዎችና ሦስት መቶ ሰረገሎች ይዞ ወጣባቸው ወደ መሪሳም መጣ። መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 14፥9
እግዚአብሔርም በአሳና በይሁዳ ፊት ኢትዮጵያውያንንመታ ኢትዮጵያውያንም ሸሹ። መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 14፥12
እግዚአብሔርም በአሳና በይሁዳ ፊት ኢትዮጵያውያንንመታ ኢትዮጵያውያንም ሸሹ። መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 14፥12
Comments
Post a Comment