ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
ኢትዮጵያዊት ጻድቅ የእምነት ሴት አርበኛ ጻድቅ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ <==
ጌታም ይህን ሁሉ መከራ እንደ መስዋዕት ቆጥሮላት አእላፍ መላእክቱን አስከትሎ መጥቶ በተስፋዋ ያመነውን ቃል ኪዳኗ የተማጸነውን እስከ 10 ትውልድ ድረስ እንዲምርላት ተስፋዋን ነግሯታል።
ጌታም ይህን ሁሉ መከራ እንደ መስዋዕት ቆጥሮላት አእላፍ መላእክቱን አስከትሎ መጥቶ በተስፋዋ ያመነውን ቃል ኪዳኗ የተማጸነውን እስከ 10 ትውልድ ድረስ እንዲምርላት ተስፋዋን ነግሯታል።
==> “የእግዚአብሔር ዓይኖች ወደ ጻድቃን ጆሮቹም ወደ ጩ...ኸታቸው ናቸውና …. ጻድቃን ጮኹ፥ እግዚአብሔርም ሰማቸው ከመከራቸውም ሁሉ አዳናቸው……የጻድቃን መከራቸው ብዙ ነው፥ እግዚአብሔርም ከሁሉ ያድናቸዋል…ጻድቃንንም የሚጠሉ ይጸጸታሉ። <== ” መዝ.፴፫፥፲፯¬-፳፩ (33፥17¬-21
==> ሀገሯ ቡለጋ ቅድስጌ ልዩ ስሙ ጥጥ ምድር አከባቢ ነው። አባቷ ቅዱስ ደረሳኒ እናቷ ቅድስት እሌኒ ይባላሉ። ቤተሰቦች በክብር በስርዓት ቅድሳት መጽሐፍትን ብሉይ ከሐዲሳት እያስተማሩ ባደገችና ለአካለ መጠን (ለአቅመ ሔዋን) ስትደርስ የመኳንንት የመሳፍንት ልጅ ናትና ለንጉስ ባለሟል ለሆኑ ትውልድ ነገዱ ፃሰርጓ ወገን ሲሆን የኢሱስ ሞዓ ልጅ ሠምራ ጊዮርጊስ ለሚባል ደግ ካህን በሕግ በ14 ዓመቷ ዳሯት። ፲፪ ልጆችም ወልዳለች።
==> ከመከራዋ ብዛት ከገድሏ ጽናት ሰውነቷ ተበሳስቶ የዓሣ መመላለሻ እስኪሆን ድረስ ከባህሩ ገብታ ወደ ግራና ቀኝ ሳትል ፲፪ ዓመት ጸለየች። በመጨረሻም ጌታ ምን አደርግልሽ ትሽያለሽ? አላት እሷም ሰው ሆኖ የማይበድል እንጨት ሆኖ የማይጨስ የለም ውሉደ አዳም እንዳይበድሉ ዲያብሎስን ማርልኝ አለችው። ከሆነልሽ ጠርተሽ አምጪው አላት ቅዱስ ሚካኤል ወስዶ ከጽንፈ ሲዖል አደረሳት። ዲያብሎስ ና ውጣ አለችው። በምድር ፈልጌ ባጣሽ ሳዝን እኖር ነበር። አሁንማ ከቤቴ መጣሽልኝ ብሎ ጎትቶ አስገባት። ቅዱስ ሚካኤልም በክንፉ ነጥቆ አውጥቷታል። ስትወጣም ስለ ገድሏ ጽናት ስድስት ክንፍ ተሰጥቷት በዚያ ነፍሳትን ማርካ ወጥታለች። በፍጻሜ ዘመኗ በቁመቷ ልክ በዓት ሰርታ ከግራ ከቀኝ ከፊት ከኋላ ጦር ተክላ ወዲያ ወዲህ ሳትል ፲፪ (አሥራ ሁለት ዓመት) በጸሎት ጸንታለች።
==> ቅድስቲቱ በደብረ ሊባኖስ ገዳም ለሰባት ዓመታት ያህል በፆም በፀሎት በተጋድሎ ከቆየች በኋላ ወደ ጣና ገዳማት በመጓዝ ከሌሎች ቅዱሳን የሚለያትን ጥያቄ ለፈጣረሪዋ አቅርባ እንደነበር ከገድሏ እንረዳለን። ቅድስት እንታችን ነፍሷን ያለ ርህራሄ የሚያስጨንቀውን ዲያብሎስን ለማስታረቅ ተነሳች። ምክንያቱም በአስፈሪው የሲዖል እሳት የሚንገበገቡት የሰው ልጆች ስቃይ አሳስቧታልና “ሳጥናኤል ይማር አለም ይዳን” ብላ ተማጸነች።
==> ጌታችንም የእናታችንን ፀሎት ሰምቶ ሳትናኤልን ሊምረው ፈቃደ ጻድቋን በቅዱስ ሚካኤል መሪነት ወደ ሲዖል ወርዳ ሳጥናኤልን ከፈጣሪ አምላካችን ታረቅ ብላ ብትጠይቀው ወደ ሲዖል ጎትቶ ቢከታት ቅዱስ ሚካኤል በብርሃን ሰይፍ ሲዖልን ቢመታው ሲዖል ከቅዲስቲቱ ክብር የተነሳ በብርሃን በተሞላች ጊዜ ብዙ ሺህ ነፍሳት በመላ ሰውነቱ ሰፈሩባት።
==> በወቅቱ ከሲዖል 10,000 (10 ሺህ) ነፍሳት አውጥታ ወደ ገነት አግብታለች። ዕለቱም ግንቦት ፲፪ (12) በደማቅ ሁኔታ ይከበራል። በእለቱም 3 ሺ ነፍሳት ታወጪያለሽ በማለት ጌታችን ቃል ኪዳን ገባላት።
==> ነፍሳትን ከሳጥናኤል ከማረከች በኋላ እመቤታችን ድንግል ማርያም ተገልጣ ቅድስቲቱን አመሰገነቻት። ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ በቁመቷ ልክ ጉድጓድ በማስቆፈር ፲፪ (12) ጦሮችን ከፊት ከኋላም በግራ በቀኝ አስተክላ ስግደት ጀመረች። ደረቷን ጀርባዋን ጎኗን ግራ ጎኗን እየወጋ በጽናት ለረጅም ዓመታት ስትጋደል ቆየች።
==> ጌታም የመአረግ ስምሽ እንደ እናቴ ማርያም ብፅኢት ቅድስት አቁራሪተ መዓልት ነው አላት። ጌታም እርፍትሽ ደርሷል ከጉድጓድ ወጥተሽ ከባሕር ቆመሽ ለምኚ ብሎ ከእርሷ ተሰወረ። እንደ ወረቀት ተበሳስቶ የነበረ ሰውነቷ ተለውጦ ቆስሎ የነበረው ሰውነቷ በሥጋዋ ታድሶ በፈጣሪ ኃይል ጸንቶ ብርሃን ለብሳና ተጎናጽፋ ከጉድጓድ በወጣች በ፲፪ (12) የጸጋ ክንፎች ተጎናጽፋለች።
==> ጌታም ይህ ሁሉ መከራዋን እንደመሥዋዕት ቆጥሮላት በቃል ኪዳኗ የተማጸነውን፣ ስሟን የጠራውን፣ በስምሽን ዝክርን ያዘከረ፣ ገድልሽን የጻፈ ያጻፈ፣ የሰማ ያሰማ በዓልሽን ያከበረ እስከ አሥር ትውልድ (12) እንዲምርላት ተስፋዋን ነግሯት ክብርት ነፍሷን ለይቶ በቃለ አቅርንት በዝማሬ መላዕክት አሳርጓታል። የዕረፍቷ መታሰቢያ ነሐሴ ሃያ አራት 24 ከተክልዬ በዓል ጋር ይታሰባል (ይከበራል) ።
==> በተጨማሪም ከባሕር ላይ ቆማ ስትፀልይ ፲ (10) አክሊል ወርዶላታል።
==> ገዳሟ ከአዲስ አበባ ወደ ደብረ ብርሃን ሲጓዙ ሸኖን አለፍ ብለን ሰንቦ ከምትባል ከተማ ስንደርስ ወደ ቀኝ ታጥፈን ጠጠራማጥርጊያ የአርበኞች ጎዳና ይዘን ስንጓዝ ቡልጋ ሀረገ ማርያም፣ ኮዩ፣ ስኮር፣ ንፋስ አምባ የሚባሉ የገጠር ከተሞችን አልፈን ሾላ ገበያ ዋና እንደርሳለን። ከመኪናችን እንደወረድን ጥቂት መንደሮችን አልፈን በረጅም ርቀት አሻግረን ስንመለከት ጉብ ባለች መጠነኛ ቦታ ላይ ችምችም ያለ አጸድ ሲመለከቱ እና እይተጠጉ ሲሄዱ ከ 800 ዓመታት በላይ እድሜ ያስቆጠሩ በኢትዮጵያዊት ጻድቅ የእምነት ሴት አርበኛ ጻድቅ ክርስቶስ ሠምራ በእጇ የተተከለ ታላቅ የቤተ ክርስቲያን ቅርስ የተጋድሎ ባዕቷንና አሁን ታቦተ ህጉ ያለበትን ትንሽ መቆኞ ይገኛል። የገዳሟም ስም ጌዬ ገዳም ሲሆን ዕድሜ ጠገብ ባለታሪክም ነው።
==> ጌታም ይህን ሁሉ መከራ እንደ መስዋዕት ቆጥሮላት አእላፍ መላእክቱን አስከትሎ መጥቶ በተስፋዋ ያመነውን ቃል ኪዳኗ የተማጸነውን እስከ 10 ትውልድ ድረስ እንዲምርላት ተስፋዋን ነግሯት ክብርት ነፍሷን ከሥጋዋ ለይቶ በቃለ አቅርንት በዝምሜ መላእክት አሳርጓታል።
የእናታችን የቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ረድኤቷ፣ በረከቷ፣ አማላጅነቷ፣ ቃልኪዳኗ፣ አይለየን አሜን።
==> ዋቢ መጽሐፍት <==
==> ገድለ ቅድስት ክርቶስ ሠምራ
==> ነገረ ቅዱሳን ቁጥር ፪፣
==> ዝክረ ቅዱሳን
==> መለከት መጽሔት

ስብሐት ለእግዚአብሔር ኪያነ ዘፈጠረ ከመ ናምልኮ
ስብሐት ለማርያም እመ አምላክ እግዝእትነ ወመድኃኒትነ
ስብሐት ለመስቀለ ክርስቶስ ዕፀ መድኃኒት ኃይልነ ወፀወንነ
ስብሐት ለማርያም እመ አምላክ እግዝእትነ ወመድኃኒትነ
ስብሐት ለመስቀለ ክርስቶስ ዕፀ መድኃኒት ኃይልነ ወፀወንነ
Comments
Post a Comment