ባለንበት ዓለም ውስጥ ለሰው ልጆች ሕይወት ጠቃሚ የሆነ ሥራ የሠሩ ብዙ ሰዎች ይገኛሉ። እኛም ባልነበርንበት ጊዜ ለአለማችን እዚህ ደረጃ መድረስ የራሳቸውን አስተዋጽኦ ያበረከቱ ታላላቅ ስመ ጥር የሆኑ ሰዎች በታሪክ ውስጥ አልፈዋል። እነዚህ ለዓለም ማሕበረሰብ ካበረከቱት አስተዋጽኦ አንጻር በሕይወት ሳሉ ብቻ ሳይሆን ከሞቱም በኃላ ስማቸው በታሪክ ማሕደርተጽፎ በየጊዜው ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተላለፈ ሲዘከር ይኖራል። የሰሩትንም ሥራ ለትውልዱ በማስተዋወቅ በክብር በማስቀመጥ ትውልድ አርያነታቸውን እንዲከተል ለማድረግ በየጊዜው ታላቅነታቸው ሲነሳ ታሪካቸው ሲነገር መስማት በዓለም ታሪክውስጥ የተለመደ ነው። በመንፈሳዊው ዓለም ደግሞ የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎች በዚህ ምድር ቆይታቸው «ሰውነቱን ሊያድናት የሚወድ ይጣላት ስለእኔ ሰውነቱን የጣላት ያገኛታል»ማቴ 10፥39 በማለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ባስተማረው ትምህርት መሰረት በኃጥአን ላይ የሚፈረድ ቅጣት፣ ለጻድቃን የሚሰጥ ዋጋ እንዳለ በመረዳት፣ ከምድራዊ ሕይወት ይልቅ ሰማያዊ ሕይወትን በመናፈቅ፣ ከኃላዬ ሊከተለኝ የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ዕለት ዕለት ይከተለኝ የሚለውን አምላካዊ መመሪያ መሰረት በማድረግ ለተጋድሎ ራሳቸውን ሙሉ በሙሉ አሳልፈው የሰጡ ቅዱሳን በየዘመኑ መነሳታቸውን የቤተ ክርሰቲያን ታሪክ በወርቃማ ብዕር ታሪካቸውን ጽፎ የምናገኛቸው የቤተ ክርስቲያን ብሩሃን ከዋክብት መስተጋድላን ብዙ ናቸው። እነዚህ ቅዱሳን ቅዱስ ጳውሎስ «ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ። ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ በዋሻና በምድር ጉድጓድ ተቅበዘበዙ»ዕብ 11፥37 ብሎ የተናገረላቸው ቅዱሳን ናቸው። ይህችን ዓለም ኃላፊ ጠፊ መሆኑን አውቀ...
Comments
Post a Comment