ሰማእቷ ቅድስት አርሴማ
በአብ ስም አምኜ፣ አብን ወላዲ ብዬ፣ በወልድ ስም አምኜ፣ ወልድን ተወላዲ ብዬ፣ በመንፈስ ቅዱስ ስም አምኜ መንፈስ ቅዱን ሰራጺ ብዬ በማመን፤ ምንም እንኳን ለአጠይቆ አካል ሦስት ብልም፤ ዓለምን በመፍጠር፣ በማሳለፍ፣ በባህሪይና በህልውና አንድ አምላክ ብዬ በማመን የእመቤታችን የቅድስተ ቅዱሳን የድንግል ማርያምንና የቅዱሳንን ሁሉ አማላጅነት አጋዥ በማድረግ አምላክ ቅዱሳን ያቃበለኝን ያህል ስለ እምነት አርበኛዋ ቅድስት አርሴማ ትንሽ እናገራለሁ።
“በእሳት ተቃጥለው በውሃ ተቀቅለዋል፤ በሰይፍ ተመትረዋል፤ በመጋዝ ተተርትረዋል፤ በመንኩራኩር ተፈጭተዋል፤ እንደ ከብት ቆዳቸው
ተገፈዋል። ወደ ጥልቅ ባሕር ተጥለዋል። በዚህ ሁሉ ከሃይማኖታቸው አላፈገፈጉም።”
የሰማዕቷ ምልጃ ፀሎት እና በረከቷ ከሁላችን ጋር ጸንቶ ለዘላለሙ ይኑር አሜን !!!!
ቅዱሳን ሰማዕታት
ቅዱሳን ሰማዕታት ማለት “እግዚአብሔርን ካዱለጣዖት ስገዱ፤ሲባሉ እግዚአብሔርን አንክድም ለጣዖት አንሰግድም፤” በማለት በዓላውያን ነገስታት ፊት ቀርበው ሳያፍሩና ሳይፈሩ ስለ ፈጣሪያቸውን የመሰከሩ ናቸው። በዚህም ምክንያት ተዘርዝሮ የማያልቅ የመከራ ዓይነትየሰማዕቷ ምልጃ ፀሎት እና በረከቷ ከሁላችን ጋር ጸንቶ ለዘላለሙ ይኑር አሜን !!!!
ቅዱሳን ሰማዕታት
ተቀብለው ለእግዚአብሔር ለፈጣሪያቸው ክብር ሲሉ ደማቸውን ያፈሰሱ፣ አጥንታቸውን የከሰከሱ ሕይወታቸውንም የሰጡ ናቸው። በእሳት ተቃጥለው በውሃ ተቀቅለዋል፤ በሰይፍ ተመትረዋል፤ በመጋዝ ተተርትረዋል፤ በመንኩራኩር ተፈጭተዋል፤ እንደ ከብት ቆዳቸው ተገፈዋል። ወደ ጥልቅ ባሕር ተጥለዋል። በዚህ ሁሉ ከሃይማኖታቸው አላፈገፈጉም። ለዚህ ነው፡- በዕብራውያን ፲፫፡፯ (13፡7) ላይ “የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው።” የተባለው።
በተጨማሪም ጌታ እራሱ በዚህ በራዕይ ፪፡፲ (2፡10) ላይም እንዲህ ሲል ተናግሯል፤ “ልትቀበለው ያለህን መከራ አትፍራ።እነሆ፥ እንድትፈተኑ ዲያብሎስ ከእናንተ አንዳንዶቻችሁን በወኅኒ ሊያገባችሁ አለው፥ አሥር ቀንም መከራን ትቀበላላችሁ። እስከሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ።” ብሏል። በይሁዳ ፩፡፫ (1፡3) ላይም “ወዳጆች ሆይ፥ ስለምንካፈለውስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።” ይላል።
ስለ ሰማዕቷ ቅደሰት አርሴማ ትነሽ ልበላችሁ.....
የጎርጎርዮስ ዘአርመንያ እኀት ናት። ዲዮቅልጥያኖስ ቆንጆ ሴት ፈልጋችሁ ስዕሏን ስላችሁ አምጡልኝ ብሎ ሰራዊቱን በየሀገሩ ሰደደ። ይሀቸ አርሴማ ከ71 ደናግለ ጋር ከተራራ ወጥታ ተቀምጣ ነበር። እየፈለጉ ሲሄዱ እሷን አይተው ስዕሏን ስለው ወስደው ሰጡት። መልካም ብላቴና አግኝታችሁልኛል ሄዳችሁ አምጡልኝ አላቸው። እርሷም አውቃ አርመንያ ወረደች፤ ይህን ሰምቶ ለንጉስ ለድርጣድስ አስፈልገህ ላክለኝ ብሎ ላከበት፤ አስፈልጎ አገኛት። እርሱም መልከ ቀናነቷን አይቶ ይህችንስ አሳልፌ አልሰጥም ብሎ መሪያቸው ‘ደርታን’ ለምኝልኝ አላት። አይሆንምያልሁ እንደሆነ ጸብ አጸናለሁ ብላ እሺ አለችው። እሷን ግን ለመንግስተ ሰማያት የታጨሽ ነሽና ይህ ዕልው እንዳያረክስሽ እወቂ አለቻት። ከዚህ በኋላ ጽዋት ልኮ ወሰዳት፤ መልኳን አይቶ በስሜት ተሸንፎ ዘሎ ያዛት። ኃይለ መንፈሳዊ ተሰጥቷታልና ጎትታ ከመሬት ቀላቀለችው። ንጉስ ነውና ቢያፍር በሰይፍ አስመታት፤ ከዚህም አያይዞ ‘ሰባ አንዱንም’ ሁሉ በሰይፍ አስመትቷቸዋል። በወንጌል ላይ “እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ፥ ጽድቅን አደረጉ፥ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አገኙ፥ የአንበሶችን አፍ ዘጉ፥ የእሳትን ኃይል አጠፉ፥ ከሰይፍ ስለት አመለጡ፥ ከድካማቸው በረቱ፥ በጦርነት ኃይለኞች ሆኑ፥ የባዕድ ጭፍሮችን አባረሩ። ሴቶች ሙታናቸውን በትንሣኤ ተቀበሉ፤ ሌሎችም መዳንን ሳይቀበሉ የሚበልጠውን ትንሣኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ፤ ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ፤ በድንጋይ ተወግረው ሞቱ፥ ተፈተኑ፥ በመጋዝ ተሰነጠቁ፥ በሰይፍ ተገድለው ሞቱ፥ ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ፤ ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ፥ በዋሻና በምድር ጕድጓድ ተቅበዘበዙ።” ዕብ.፲፩፡ ፴፫-፴፰ (11፡33-38 ያለው ይፈጸም ዘንድ ይህን ሁሉ መከራ ተቀበሉ። ኋላ ግን መልኳ ትዝ እያለው እህል ውሃ የማይቀምስ ሆነ። ወዳጆቹ ነገሩን እንዲረሳ ብለው አደን ይዘውት ወጡ። በዚያ እሪያ ሆኖ ቀርቷል። የንጉሱ እህት ጎርጎርዮስን ወንድሜን አድንልኝ ስትለው አጽመ ቅዱሳንን አሳዩኝ ብሎ አሳይታው ያን አስቀብሮ ካለበት ሄዶ “ባድንህ በፈጣሪ ታምናለህ?” አለው።እርሱም በአዎንታ እራሱን ነቀነቀ። የተደረገለትን እንዳይዘነጋ ከእጁ ከእግሩ የእርያ ምልክት ትቶ ጸልዮ አድኖታል። ኋላም አምኛለሁ አጥመቀኝ በማለቱ ቢጠይቀው ሥልጣን የለኝም አለው፤ በአንጾኪያው ሊቀ ጳጳስ እጅም ተጠመቀ። እርሱንም ሊቀ ጳጳስነት አስሹሞ ብዙ ተግሳጻትን ጽፎ ብዙ ድርሳናትን ደርሶ ብዙ የቱርፋት ሥራ ሠርቶ አርፏል።እረፍቱም ታህሳስ 15 ቀን ነው። ቅድስት አርሴማ ግን በዚህ ሁሉ ተጋድሎዋ እግዚአብሔር የገባላት ቃል ኪዳን በእኔ ስም አምነሽ የዚህ ዓለም ተድላና ደስታ ሳያታልልሽ አንገትሽን ለሰይፍ ሰጥተሽ ተሰይፈሻል፤ የሰማዕትነት ተጋድሎ ፈጽመሻልና ስምሽን የጠራ፤ በዓልሽን ያከበረ፤ ዝክርሽን የዘከረ፤ ገድልሽን የጻፈና ያጻፈ፤ የሰማና ያሰማም እስከ ፲፪ ትውልድ ድረስ እምርልሻለሁ’’ ሲል ቃል ኪዳን ገብቶላታል፡፡ በዚህም መሠረት በሷ አማላጅነት አምኖ ገዳሟም ሄዶ በጸሎት የተማጸናት ሁሉ ለችግሩ መፍትሄ አግኝቶ እንደሚመለስ እሙን ነው። የሰማዕቷ ረድኤት በረከት ይጠብቀን አሜን፡፡
ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣኝ፣ ካለማወቅ ወደ መረዳት ያደረሰኝ አነሳስቶ ላስጀመረኝ አስጀምሮ ላስፈጸመኝ ጥንት ላሌለው ቀዳማዊ ፍጻሜ ላሌለው ድህራዊ ያልኖረበት ጊዜ የሌለ የማይኖርበት ጊዜም የማይኖር የዘላለም ንጉስ ሁሉን ቻይ ፈጣሪ እግዚአብሔርን በራስ ፀጉሬ ቁትር በአጥንቶቼም ልክ አመሰግናለሁ፡፡ እድሜ ለንሰሐ ዘመን ለፍሰሃ ሰጥቶኝ ይህችን ታህል ስለ አባታችን እንድመሰክር የረደኝ አምላክ ስሙ የተመሰገነ ይሁን።
አመስግኛት የማልሰለች፣ ስለሷ ተናግሬ የማይደክመኝ፣በሰማይ ያሉ መላእክት በምድርም የሚኖሩ የአዳም ዘር ሁሉ የሚያመሰግኗት በአማላጅነቷ ሁል ጊዜ የማትለየኝ ከፀሐይ ሰባት እጅ የምታበራ የብርሃን እናት የሁሉ እመቤት የአምላክ እናት ከተመረጡ የተመረጠች ከተለዩ የተለየች ከተከበሩ የተከበረች እናቴ እመቤቴ ድንግል ማርያም በቃላት ልገልጸው ከምችለው በላይ አመሰግናለሁ፡፡
የእግዚአብሔር፣ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት፣ የጻድቃን፣ የሰማዕታት፣ የቅዱሳን ሐዋርያት፣ የቅዱሳን አበው መነኮሳት፣ የቅዱሳት አንስት፣ የደናግላንና የቅዱሳን ሁሉ ምልጃና ቃል-ኪዳናቸው ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን ይቆየን፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ለዘበቅዱሳኒሁ ይሴባሕ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለም ዓለም አሜን፡፡ ወአሜን ለይኩን ለይኩን፡፡ አነሳስቶ ያስጀመረኝ አስጀምሮ ያስጨረሰኝ የቅዱሳን አባቶቻችን አምላክ ይክበር ይመስገን አሜን፡፡
ምንጭ፡- ነገረ ቅዱሳን ቁ.፩፣ መዝገበ ታሪክ ቁ.፩፣ ስንክ ሳር ዘታህሳስ መልከአ ቅ/አርሴማ
Comments
Post a Comment